የመድብለ ባህላዊ ቪክቶሪያ

በዓለም ውስጥ በአንደነት ከሚኖሩና በጣም የተሰባጠረ ህብረተሰብ ካላቸው ሃገሮች መካከል ቪክቶሪያ አንዷ ናት። 260 ቋንቋዎችና የአካባቢ መግባቢያዎች እንዲሁም 135 የተለያዩ እምነቶች ካሉባቸው ከ200 ሃገሮች በላይ የመጣን ነን።

የቪክቶርያ መንግሥት፣ ባህላቸው፣ ቋንቋቸው ወይም የሃይማኖት ጀርባቸው ምንም ይሁን ምን፤ ሁሉንም ሰው የሚያሳትፍ በእኩልነት ግልጋሎቶችን የሚያገኝበት መድብለ ባህላዊ ማህበረሰብ እንዲኖር ይደግፋል።

የቪክቶርያ መንግሥት በሚከተሉት መንገዶች የመድብለ ባህላዊ ማህበረሰቦችን መደገፍ ይፈልጋል፡

  • ለማህበረሰብ ድርጊቶች የገንዘብ እርዳታ፣ ለአዛውንት ቡድኖች፣ የመዋቅር ድጋፍ፣ የማህበረሰብ የቋንቋ ትምህርት ቤቶችና ሌሎች ተነሳሽነቶችን፣
  • የግንባታ የገንዘብ እርዳታና ለህንፃ መገልገያ የሚሆን ቁሳቁስ፣
  • እንደ ሰፈራ የመሳሰሉትን ፍላጎቶችና የማህበረሰብ የተነሳሽነት ጉዳዮችን መደገፍ፣
  • የባህልና የእምነት የመተባበርን ተነሳሽነቶችን በመደገፍ የባህልና የሃይማኖት ስብጥርን እንዲሁም የህብረተሰብ መቻቻልን ማዛመት ናቸው።

የተዘረዘሩትን ጨምሮ፣ ስብጥርነታችንን በተለያዩ ሂደቶች እናከብራለን፡ የከንቲባው ታላቅ የእራት ግብዣ፣ (Premier’s Gala Dinner) የባህል ስብጥር ሳምንት (Cultural Diversity Week) የቪክቶሪያ ቪቫ የመድብለ ባህላዊ በዓል (Viva Victoria Multicultural Festival) እና የቪክቶሪያ የመድብለ ባህላዊ መልካም ድርጊት ሽልማት (Victoria’s Multicultural Awards for Excellence)።

በቋንቋዎ መረጃ ከፈለጉ በድረገጽ ይመልከቱ።

Events Calendar

There are no upcoming events at this time.

find more events here >